ታላቁ እስክንድር ሲሞት ጄኔራሎቹን ጠርቶ ሦስቱን የመጨረሻ ምኞቱን ነገራቸው።
1. የሬሳ ሳጥኔን መሸከም ያለባቸው በጣም የተሻሉ ዶክተሮች ብቻ ናቸው።
2. ሀብቴን ወደ መቃብር ስትወስዱኝ መንገድ ላይ በትኑት።
3. ሁሉም ሰው እንዲያየው እጆቼን በንፋስ እንዲንጠለጠሉ ተውአቸዉ።
ጄኔራሎቹ ደንግጠው እንዲያብራራላቸው ጠየቁት።
ታላቁ እስክንድር እንዲህ ሲል መለሰ፡- እኔ ዶክተሮች የሬሳ ሳጥኔን እንዲሸከሙ እፈልጋለሁ ምክንያቱም ምርጥ ዶክተሮች እንኳን በሞት ፊት መፈወስ የማይችሉ መሆናቸውን ለማሳየት ነው።
በምድር ላይ የተገኘ ሀብት፣ በምድር ላይ እንደሚቀር ሁሉም ሰው እንዲያይ መንገዱ በሀብቴ ተበታትኖ እንዲረማመዱበት እፈልጋለሁ።
ባዶ እጃችን እንደተወለድን ሰዎች እንዲረዱ እና በጣም ውድ የሆነው ነገር ካለቀ በኋላ ባዶ እጃችንን እንድንተወው እጄ በነፋስ ውስጥ በነፃነት እንዲወዛወዝ እፈልጋለሁ።
እንግዲያው፣የተሰጡን ነገሮች ዋጋን እንወቅ፣ጊዜ ከሁሉ የላቀው አስተማሪ ነው፣ እግዚአብሔር የሰጠን እጅግ ውድ ነገር እርሱ ነው።ጊዜ ከማለፉ በፊት በጥበብ እንጠቀምበት።
በቶለሣ ደረሱ ከFB