ፊደል

መሰላል ነው ፊደል ተራራ መዝለቂያ፣

ከስምጥ የመለየት የጨለማ ማብቂያ፡፡

ድልድይ ነው ፊደል ወንዝ መሻገሪያ፣

ከበርባኖስ ጥቁረት ብርሃን መጭለፊያ

የፊደል ገበታ የቆጠርኩኝ ለታ፣

የዓለማት ጥቁረት መግነዙ ተፈታ፡፡

መማር ነው ቀመሩ ፊደል ነው ድልድይ፣

ጥቁረትን ለጠሉ፣ ትናንት ላይ ቆመው የሩቁን ለሚያዩ፡፡

ያለማወቅ ፅልመት ጉልበቱ ሚሰበር፣

በፊደል ብርሃን ነው ሞቱ የሚበሰር፡፡

እንማማር ዛሬ እንማማር ነገ፣

ትምህርት ነው ሀገር ያሳደገ፡፡

በመ/ር ታደሰ ዘጎንቻ በድጋሚ የተወሰደ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top